የዘንድሮ የዓለም አካባቢ ቀን “Climate Action’’ በሚል መሪ ቃል በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ53ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ33ኛ ጊዜ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ተከብሯል። በየዓመቱ ግንቦት 28 የሚከበረውን የዓለመቀፍ አከባቢ ጥበቃ ቀን አከባበር አስመልክቶ በዓሉ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በዱራሜ ከተማ ተከብሯል።
የደን አካባቢ ጥበቃና ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የአከባቢ ጥበቃና ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሎለሞ ሱላሞ “Climate Action’’የሚለው መሪ ቃል ለሀገራችንና ክልላችን ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑን አመላክተው ለአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ በአብይ ጉዳዮች ላይ ትክረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ደን አካባቢ ጥበቃና ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብርሃም መጫ የአየር ንብረት ሁኔታንና የበዓሉን አስፈላጊነትን አስመልክተው ሀገራችን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሙቀት አማቂ ጋዝ ልቀት የምታበረክተው አስተዋጽኦ ከ 0.5% በታች ቢሆንም፣ በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ለሚከሰቱት ተደጋጋሚ ድርቅ፣ ጎርፍ፣ የመሬት መንሸራተት፣ የደን መመናመንና የመሬት መራቆት በእጅጉ አሳሳቢ እንደሆነ ገልፀዋል ። ኃላፊው እነዚህ ተግዳሮቶች በዝናብ ጥገኛ በሆነው ግብርና፣ በምግብ ዋስትና፣ በውሃ ሀብታችን እና በገጠሩ ማኅበረሰብ የኑሮ ሁኔታ ላይ ቀጥተኛ ስጋት እያስከተለ እንደሆነም ኃላፊው አመላክተዋል። አቶ አብርሃም የ2018 ዓ.ም ትኩረት የችግኞች ፅድቀት መጠን ማሻሻል፣ ዘላቂ የተፋሰስ ልማት እና የረጅም ጊዜ ሥነ-ምህዳራዊ ጥቅሞችን ማረጋገጥ መሆኑን ገልፀዋል ።
ኃላፊው ቢሮው የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም (climate-smart) አሠራሮች መሸጋገር አስፈለጊነት ላይ በትኩረት እየሠራ እንደሆነ ገልፀው የከተሞች ጽዳትና ውበት፦ የቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ እና የከተማ አረንጓዴ መሠረተ-ልማትን ማጠናከር እና ከከተሞች የሚወጣውን የሙቀት አማቂ ጋዝ ልቀት በመቀነስ አካባቢን መጠበቅ እንደሚገባም አሳስበዋል ።