የአካባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ ዘርፍ ዋና ዋና ተግባራት፡
በአካባበቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ ሥራዎች ላይ ለባለድርሻ አካላትና ለማህበረሰቡ ግንዛቤ መፍጠር፤
የአካባቢ ብክለት (የድምጽ፣ የአየር፣ የአፈር፣ የፕላስቲክ እና የውሃ) ሥራዎችን መከታተልና መቆጣጠር፤
የኬሚካል ማምረቻ እና ማከማቻ ተቋማት ኢትዮጵያ በተቀበለቻቸው ዓለምአቀፍ ስምምነቶችና አገራዊ ህጐች መሠረት እንዲፈፀሙ መከታተልና መቆጣጠር፤
በተለያዩ የማምረቻ እና አገልግሎት መስጫተቋማት ላይየክትትል ሥራዎችን መሥራትና ህግን ማስከበር፤
ለተለያዩ ለግልና ለመንግሥት ልማት ፕሮጄትቶች የአካባቢና ማህበራዊ ተጽዕኖ ግምገማ የይሁንታ ሥራ ፈቃድ መስጠት፤
የአካባቢና ማህበራዊ አያያዝ እቅድ የይሁንታ ሥራ ፈቃድ መስጠት፣
የአካባቢና ማህበራዊ ክዋኔ ኦዲት ማካሄድ፣
በአካባቢ ጉዳት ላይ ለሚቀርቡ ቅሬታዎች ምላሽ መስጠት፤
በአረንጓዴ ቴክኖሎጂ አባወራ/ እማወራ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሙያዊ ድጋፍ ማድረግ፤