Skip to main content
005

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከ530 ሚሊዮን በላይ ዓለማ ተኮር የችግኝ ተከላ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ደን አካባቢ ጥበቃና ልማት ቢሮ ገለፀ ። (ዱራሜ፣ ሰኔ 13/2018 ዓ.ም) በ2018 ዓ.ም "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሃሳብ ለሚከናወነው ለአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ከ530 ሚሊዮን በላይ ዓለማ ተኮር የተለያዩ ችግኝ ተከላ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ደን አካባቢ ጥበቃና ልማት ቢሮ አስታውቋል ። የቢሮው ምክትል ኃላፊና የደን ጥበቃና ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አድማሱ ወልደማሪያ እንደ ገለፁት የተለያዩ ዘርፈ ብዙ ማህበረ_ኢኮኖሚያዊና ስነ ምህዳራዊ አንድምታ ያላቸዉ ዓለማ ተኮር ችግኞች ለተከላ መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል ።

የተከላ መሬት ዝግጅቱ በሼፕ ፋይል የመረጀ አያያዝ ቴክኖሎጂ የተደገፈ ለተከላ የደረሰ የደን ፣ የቀርከሃ እና የዉበት ዛፍፎች ችግኝ ዝግጂት መደረጉን ያመላከቱት ኃላፊው የተከለ መሬት እና የጉድጓድ ዝግጂት መደረጉንም ገልጸዋል ። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ደን አካባቢ ጥበቃና ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብርሃም መጫ የደን ዓላማን መሠረት ባደረገ መልኩ ለ2018 ለደንና አግሮፎረስተሪ ችግኝ ተከላ የሚያስፈልጉ ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቃቸውን አመላክተዋል ። የደን ሽፋን ለማሳደግ በተደረገው ባለፉት ሰባት ተከታታይ ዓመታት የችግኝ ተከላ ክንዋኔ የክልሉን ሕዝብ ያሳተፈ የንቅናቄ ስራዎች ስከወኑ እንደቆዩም አቶ አብርሃም አመላክተዋል። 

ዓላማ ተኮር የደን ሽፋን ማሳደግ የአካባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ ከመታደግ ባሻገር በግብርናው ዘርፍ ከምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ጋር ተያይዞ የተጋረጡ የምርታማነት መናቆን ከመቀነስ ረገድም ዕምርታ እንዳመጣም አቶ አብርሃም ገልፀዋል ። የደን ዛፍ የዘርፉን የገቢ ምርትን የሚተኩ፣ ለኢንዱስትሪ በቂ ምርት የሚቀርብባቸው የስራ ዕድል ከመፍጠር አንፃር፣ በዘርፉ ወጪ ምርትን ከማበረታታት ረገድ ባሻገር በሃገራዊ ምጣኔ ሀብትና በብሄራዊ ጥቅል ምርት ዕድገት ላይ የተሻለ ድርሻ እንዳበረከተውም ኃላፊው ገልጸዋል። ኃላፊው በ2018 "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሃሳብ ለሚተገበረው ለክልላቀፍ የአረንጓዴ አሻራና ችግኝ ተከላ ተግባር የሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ እንደሚጠበቅም አሳስበዋል

Add new comment

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.